የዳያስፖራ አደረጃጀቶች የእውቅና መርሐግብር ዛሬ ይካሄዳል

262

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 18/2015 ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ እያደረገ ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ እና በጎ ተሳትፎ እውቅና የሚሰጥበት መርሐግብር ዛሬ ይካሄዳል።

በመርሐግብሩ ላይ ለሚካፈሉ አመራሮችና ተወካዮች የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ እና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

May be an image of 7 people and people sitting

የእውቅና ስነ ስርዓቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የዳያስፖራ አባላት በተገኙበት እንደሚከናወን አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም