በየዋሂል ገጠር ቀበሌ በ14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የተገነባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ተዘጋጀ

167

ድሬዳዋ (ኢዜአ) ጥር 17/2015 በድሬዳዋ የዋሂል ገጠር ቀበሌ በ14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የተገነባ የዋሂል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደረገ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ዛሬ ትምህርት ቤቱን መርቀው ከፍተዋል።

ከንቲባ ከዲር ጁሀር በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የገጠሩን ህብረተሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድን ጨምሮ የካቢኔ አባላትና የገጠር ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም