የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ተጀምሯል

67
አዲስ አበባ መስከረም 23/2011 11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ድርጅታዊ ጉባኤ ተጀምሯል። የደኢህዴን ሊቀ-መንበር  ወይዘሮ ሙፍሪያት ከሚል የደቡብ ክልል "ይህን በታሪክ የትግል ምዕራፍ ወቅት የሚካሄድ" ጉባኤ በማዘጋጀታችን የላቀ ደስታ ይሰማናል ብለዋል። ጉባኤውም የህዝቦችን አንድነትና ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር፤ በሂደቱ የነበሩትን ጉድለቶችንና ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ተግዳሮቶች ነቅሶ በማውጣትም የጀተመረውን የህዳሴ ጉዞ ወደላቀ ምዕራፍ የምናሸጋግርበት ይሆናል ነው ያሉት። የዘንድሮው የጉባኤው መሪ ቃል "አገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና" የሚል ሲሆን በጉባኤው ትልልቅና ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ውሳኔ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም