የአዴፓ ሊቀ መንበር ለመላው የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ምስጋና አቀረቡ

71
አዲስ አበባ መስከረም 22/2011 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ላለፉት አምስት ቀናት በባህር ዳር ያካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ በስኬት በመጠናቀቁ ሊቀ መንበሩ ለመላው አባላትና ደጋፊዎች ምስጋና አቀረቡ። ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉት የክልሉና የኢትዮጵያ ህዝቦችም በአዴፓ ስም አመስግነዋል። ሊቀመንበሩ አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት 12ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በአዲስ መንፈስ የክልሉን እና የአገሪቷን የለውጥ ጉዞ ቀጣይነት ከፍታውን አስጠብቆ ለመምራት የሚያስችሉ ውሳኔዎችን አሳልፏል፤ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል። እነዚህን ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች በተሟላ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ለውጡን በተሻለ ፍጥነት እና ጥራት በጋራ ማስቀጠል ይቻል ዘንድ ሁሉም እንዲተጋ ሊቀ መንበሩ ጥሪ አስተላልፋለሁ። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በ12ኛው ጉባኤ 13 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ሲመርጥ፤ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የድርጅቱ ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም