ለ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የቅደመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቋል

106
መስከረም 22/2011 ከነገ ጀምሮ ለሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁ ተገልጿል። ጉባኤውን አስመልክቶ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአጋር ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ተሰማ  ዛሬ በሀዋሳ በሰጡት  ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት ነገ ለሚካሄደው ጉባኤ የሚያስፈልጉ  ቅድመ ዝግጅቶች ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀዋል፡፡ ጉባኤው ሰላምን ፣ ይቅርታን ፣ መደመርን ፣ የሀሳብ ብዝሀነት ን፣ አንድነትንና  የአገር እድገትን  በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ  እንደሚመክር ነው አስተባባሪው ያሳወቁት። ጉባኤው በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ እንዲፈጸሙ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ገምግሞ  የቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በጉባኤው 2 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን አንድ ሺህ በድምጽ  ቀሪዎቹ  አጋር ድርጅቶች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የውጭና የሀገር ውስጥ ተጋባዥ እንግዶች እንደሆኑም  ተገልጿል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም