የአየር ኃይል ነባር የሙያ ማሻሻያ ያደረጉ አባላትንና አዲስ መሰረታዊ ወትድርና ያጠናቀቁ ምልምሎችን እያስመረቀ ነው

282

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 4/2015 የኢፌዴሪ የአየር ኃይል በደረጃ-7 የሙያ ማሻሻያ ያደረጉ የአየር ኃይል ነባር አባላትን እና አዲስ መሰረታዊ ወትድርና ያጠናቀቁ የአየር ኃይል ምልምሎችን እያስመረቀ ይገኛል።

በምርቃት መርኃ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች የአየር ኃይል መኮንኖች እና እንግዶች ተገኝተዋል።

የምርቃት መርኃ-ግብሩም የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና መምሪያ ቅጥር ግብ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም