በመጪዎቹ አስር ቀናት ዝናብ ሰጪ ሁኔታ በአብዛኛው በደቡብና በምዕራብ አጋማሽ ይኖራል

57
አዲስ አበባ መስከረም 22/2011 በመጪዎቹ  አስር ቀናት ዝናብ ሰጪ ሁኔታዎች በአብዛኛው በደቡብና በምዕራብ አጋማሽ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደሚኖር የብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በደቡብና በምዕራብ አጋማሽ የኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ የተሻለ ገጽታ ሊኖራቸው እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ። በአጠቃላይ በሚቀጥለው ወር ለእነዚህ አካባቢዎች ላይ የተሻለ ዝናብ ሰጪ ሁኔታ ሊኖራቸው እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች በማሳየታቸው ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችል ኤጀንሲው ጠቁሟል። የክረምት ወቅት ዝናብ በምዕራብ አጋማሽ ላይ የሚቀጥል ሲሆን ወደ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ሊስፋፋ እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቃማ የአየር ሁኔታ እንደሚያመዝን የሚጠበቅ ሲሆን አልፎ አልፎ ከሚኖረው እርጥበታማ ሁ የአየር ሁኔታ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊያገኙ ይችላሉ። በዚህም ከኦሮሚያ ጅማ፣ ኢሊአባቦር፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ የቦረናና ጉጂ፣ አዲስ አበባ፤ ከሶማሌ ሲቲ፣ ጂግጂጋ፣ ደገሀቡር፣ ፊቅ እና ጎዴ፤ ከደቡብ ክልል የወላይታ፣ ዳውሮ፣ ጋሞ ጎፋ፣ ከፋና ቤንች ማጂ፣ የሰገን ህዝቦች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳና ካማሺ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ዞን 1፣ 2 እና4 ከአማራ የምዕራብ ጎጃም፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ አገዋዊ፣ በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር ተቀራረበ ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በተጨማሪም አርሲና ባሌ፣ ምስራቅ ሀርረጌ፣ የድሬዳዋና ሀረሪ አልፎ አልፎ ከሚፈጠሩ ደመናዎች አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። የተቀሩት የአገሪቱ ስፍራዎች ደረቅ ሆነው ይቆያሉ። በምዕራብ አጋማሽ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ለግብርና ዘርፍ ጠቃሜታ ይኖረዋል፣ ለሰብሎች እና ተክሎች አወንታዊ ሚና ይኖራቸዋል። በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ አካባቢዎች የማሳ ዝግጅት ለማድረግና ዘር ለመዝራት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣ ከዚህም በተጨማሪ ለአብርቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የኤጀንሲው መረጃ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም