ሀገር አቀፍ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተካሄደ

152

አዲስ አበባ /ኢዜአ/ ታህሳስ 13/2015 ሀገር አቀፍ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ ።

በማስጀመሪያ ኘሮግራሙ ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ፤የአዲስ አበባ ጤናቢሮ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ የሀይማኖት አባቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የማስጀመሪያ ኘሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ድጉማ ባስተላልፍት መልእክት እንደገለፁት፤በሽታው ባለፉት 3 ወራት በስፋት መታየቱን ሲያስረዱ በተለይም በድርቅ እና በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም በሀገር አቀፍ ጀረጃ 15.5 ሚሊየን እድሚያቸው ከ 9ወር እስከ 5 አመት ለሆናቸው ህፃናት እንደሚሰጥ ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ጤናቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ በበኩላቸው፤በአዲስ አበባ ደረጃ 520ሺ ህፃናት ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

ክትባቱም ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 10ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም