የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

125
መስከረም 20/2011 የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ አባገዳ ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶች ሴቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላዊ አልባሳትን  በመልበስና እርጥብ ሳር በመያዝ እያከበሩት ይገኛሉ፡፡ በዓሉ በሚከበርበት ቢሸፍቱ ከተማ አርሲዴ ሀይቅ ዳርቻ  በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ተገኝቷል። ዘንድሮ የሚከበረው “የኢሬቻ በዓል ኢሬቻ ለፍቅርና ለአንድነት”  በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ሲሆን በበዓሉ ላይ የተገኙ ታዳሚዎች ልዩ ልዩ ጭፈራዎችን በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ በበዓሉ ላይ በብዛት የተገኙት ወጣቶች ሲሆኑ ወጣቶቹ ባህላዊ አልባሳትን በማድረግ በድምቀት እያከበሩት ነው፡፡ በዓሉ ያለምንም ስጋት በነጻነት እየተከበረ እንደሚገኝናወጣቶችም  በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር  በቀናጀት የህብረተሰቡን ደህንነት እያስከበሩ ይገኛል፡፡ በበዓሉ ላይ ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የተከበረ ሲሆን ሠላም ፣አንድነትና ፍቅር የተንፀባረቀበት ነው። ዛሬ ከለሊቱ 10 የተጀመረው የኢሬቻ በአል አከባበር  በሰላማዊ መንገድ  እተከበረም ነው፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም