የኢትዮጵያ አየር መንገድ “በ2022 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ዘርፍ” ቀዳሚ በመሆን ተሸለመ

114

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 4/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግሎባል ትራቭለር መጽሔት “በ2022 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ዘርፍ” ቀዳሚ በመሆን ተሸለመ።

የአሜሪካው “Global Traveler” መፅሔት ከመንገደኞች በሚያሰባስበው ድምፅ የተለያዩ እውቅናዎችን ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት በሚያበረክተው የእውቅና ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የ2022 ዓ.ም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።

May be an image of text that says "Global Traveler. North America Latin America Vote Now Staff StaffBlog S7 Airlines Caribbean Europe in Africa in Middle East Asia Oceania Best Airline in Africa 1. Ethiopian Airlines 2. Royal Air Maroc Kenya Airways Air Seychelles .Air Mauritius"

በዘርፉ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥሎ ሮያል ኤይር ሞሮኮ፣ ኬኒያ ኤይር ዌይስ፣ኤይር ሲሼልስ እና ኤይር ሞሪሽየስ በቅደም ተከተል ከሁለት እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም