በአሜሪካ ኦሃዮ የሆኖሉሉ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
በአሜሪካ ኦሃዮ የሆኖሉሉ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸነፉ
153
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 3/2015 በአሜሪካ ኦሃዮ የሆኖሉሉ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸንፈዋል።
በኦሃዮ ግዛት ሆኖሉሉ የባህር ዳርቻ በተካሄደው 50ኛው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቀዳሚነት አጠናቀዋል።
በውድድሩ አትሌት አሰፋ መንግስቱ 2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ አንደኛ በመሆን አጠናቋል።
ኬኒያዊው በርናባስ ኪፕቱም እና ጃፓናዊው ዩሂ ያማሽታ ሁለተኛና ሶሰተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሴቶች መካከል በተደረገው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሳየች አያሌው 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 58 ሴኮንድ በመግባት በአንደኝነት ስታጠናቀቅ ሌላኛዋ አትሌት አበበች አፈወርቅ 2 ሰዓት ከ34 ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ በመግባት 2ኛ ሆናለች።
በውድድሩ ጃፓናዊቷ ኤሪ ሱዝኪ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
በዚህ ውድድር በቀዳሚነት ያጠናቀቁት አትሌቶች እያንዳንዳቸው 25 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል።