የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የቀረቡለትን 10 አባላት ተቀብሎ አጸደቀ

236

ሀዋሳ (ኢዜአ) ህዳር 30 ቀን 2015 በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የብልፅግና ፖርቲ አንደኛ ጠቅላላ አስቸኳይ ጉባኤ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲካተቱ የቀረቡለትን 10 አባላት ተቀብሎ አፀደቀ።

ጉባኤው በዛሬ ከሰዓት ውሎው በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብርሃም አለኽኝ አቅራቢነት በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲካተቱ የተመረጡ አባላትን ተቀብሎ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት የብልፅግና ፖርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆነው የተካተቱት ጁል ናንጋል ከጋምቤላ፣ ቀበሌ መንገሻ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች፣ መስከረም ደበበ ከኦሮሚያ ፣ ታደሰ ገብረ ፃዲቅ ፣ አብርሀም አያሌው፣ ዲያቆን ተስፋሁን ባንተያብል፣ ደሳለኝ ጣሰው፣ ወርቁ ሃይለማርያም፣ ዘውዱ ማለደ እና መሀመድ ያሲን ከአማራ ክልል ናቸው።

አቶ አብርሀም ለጉባኤው እንዳስረዱት ፤ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲካተቱ የተደረገው ምርጫ ቦርድ እንዲስተካከል ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ በፖርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ ( ሸ) መሰረት የተከናወነ ነው።

ጉባኤው በተጨማሪም 11 የፖርቲውን ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን አባላትን ምርጫ አካሄዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም