የማይጨው ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች

113

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 30/2015 የማይጨው ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ያገኘው ከአላማጣ-ማይጨው የተዘረጋው የ66 ኪሎ ቮልት የሃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተከናውኖ በመጠናቀቁ ነው።

በቀጣይ ሌሎች ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው አካባቢዎች መልሰው እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም