ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የአውሮፓ አገራት ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሰጡ

144

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 30/2015 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በሰላም ስምምነቱ ትግበራ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በመንግስትና በህወሃት መካከል በተደረገው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰላም ስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ እርዳታ በማቅረብና መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማስጀመር ረገድ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውንም አብራርተዋል።

በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችንና ጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም