በሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር የተመራ የልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

95

አዲስ አበባ ሕዳር 28 ቀን 2015 (ኢዜአ) በሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልከድር መሃመድ ኑር የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ መኳንንቴ አቀባበል ማድረጋቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የልዑካን ቡድኑ ለሦስት ቀናት በሚያደርገው የስራ ጉብኝት ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይና ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በመገናኘት በቀጠናዊ የሰላም እና ደህንነት ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም