ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ከፍተኛ ሃላፊ ጋር ተወያዩ

134

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 27 ቀን 2015 ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት የስርዓተ ምግብ ከፍተኛ ሃላፊ ጌርዳ ቨርበርግ ጋር ተወያዩ ።

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ከፍተኛ ሃላፊ ጌርዳ ቨርበርግን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸውም በኢትዮጵያ በምግብ እና ሥርዓተ ምግብ፣ የምግብ ሥርዓተ ትራንስፎርሜሽን እና የሰቆጣ ቃልኪዳን አተገበር ላይ ያተኮረ ነበር።

ኃላፊዋ መንግሥት በሥርዓተ ምግብ ሥራዎች አተገባበር ላይ ያለውን ቁርጠኝነት፣ በተለይም በሚኒስቴር መሥራያ ቤቶች መካከል ያለው ቅንጅታዊ አስራር እንዳስደነቃቸው ገልጸው ፕሬዚደንቷ የአገር አቀፉ የሥርዓተ ምግብ ሻምፕዮን እንዲሆኑ ጥያቄ አቅርበዋል።

ፕሬዚደንቷም በበኩላቸው ኢትዮጵያ በ2023 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚያዘጋጀውን የሥርዓተ ምግብ ዓለምአቀፋዊ ጉባኤ የማዘጋጅት ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸውን ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም