ኢትዮጵያ እንግዶችን የተቀበለችበትና ያስተናገደችበት መንገድ የሚደነቅ ነው--የዓለም አቀፉ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተሳታፊዎች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እንግዶችን የተቀበለችበትና ያስተናገደችበት መንገድ የሚደነቅ ነው--የዓለም አቀፉ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተሳታፊዎች
160
አዲስ አበባ (ኢዜአ)ህዳር 24/2015 ኢትዮጵያ እንግዶችን የተቀበለችበትና ያስተናገደችበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን የ17ኛው ዓለም አቀፉ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ የተካሄደው 17ተኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ትናንት ተጠናቋል፡፡
በተባበሩት መንግስት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በተካሄደው የጉባኤው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የጉባኤው ተሳታፊዎች ቆይታቸውን በተመለከተ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ እግዶቿን የተቀበለችበት መንገድ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በጉባኤው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማእከል ከመሆን ባሻገር ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በብቃት ማስተናገድ የምትችል ሀገር መሆኗን በተግባር ማሳየቷንም ነው የገለጹት፡፡
ቆይታቸው አስደሳች እንዲሆን ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ የማይበገር ኢንተርኔት ለዘላቂና እኩል የጋራ ተስፋ" በሚል መሪ ሀሳብ ባለፉት አምስት ቀናት በዘርፉ ባሉት እድሎችና ተግዳሮቶች ዙሪያ ሲመክር የቆየ ሲሆን፤ ጉባኤው በተነሱ ጉዳዮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት ተጠናቋል፡፡