ኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና ዘላቂ ሰላምን መገንባት የዘወትር ተግባራቸው ሊሆን ይገባል- የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት

139

አዲስ አበባ (ኢዜአ)  ህዳር 23/2015  ኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና ዘላቂ ሰላምን መገንባት የዘወትር ተግባራቸው ሆኖ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አደም ፋራህ ተናገሩ።

የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አመራርና  ሰራተኞች 17ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን አከበሩ።

No photo description available.

በመርሃ ግብሩ ላይ  የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንትና የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አደም ፋራህ እንዲሁም የፓርቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የቀኑ መከበር ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከርና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት መሰረት የሚጥል ነው።

ህዝቦች ባህላቸውንና ታሪካቸውን እንዲያስተዋውቁ በሚፈጥረው ምቹ ሁኔታ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።

ይህንን ህብረብሔራዊ አንድነትን ለመናድ በርካቶች የተሳሳቱ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር እኩይ አላማቸውን ለማስፈጸም እየሰሩ እንደሚገኙም አክለዋል።

የውስጥ ጉዳዮችን በራስ አቅም በመፍታት የነዚህን እኩይ አላማ ማክሸፍና ዘላቂ ሰላምን መገንባት የሁላችንም ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የፊታችን ህዳር 29 በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት "ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል ይከበራል"።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም