ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያዩ

217

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 22/2015 ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያዩ።

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጉቴሬዝ ቀደም ብለው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን ኢትዮጵያና የመንግስታቱ ድርጅት ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በመቀጠልም ከፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የውይይታቸውም ትኩረት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም