የክልሉን ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም የሚገመግም መድረክ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

177

ባህር ዳር (ኢዜአ) ህዳር 21/2015 በአማራ ክልል በመገንባት ላይ የሚገኙ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የሚገመግም መድረክ በባህር ዳር በመካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶና የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሚኒስተር ዴኤታው ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በአማራ ክልል እየተገነቡ ከሚገኙ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል “ከተወሰኑት በስተቀር የበርካቶቹ አፈጻጸም ከታቀደለት ጊዜ ጋር ሲተያይ መጓተት ታይቶባቸዋል”።

የአፈጻጸም ግምገማው መድረክ አላማም ለፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም መጓተት መሰረታዊ ምክንያቶችን መለየትና የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በመገንባት ለይ ከሚገኙ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል፣ የላይኛውና ታችኛው ርብ የመስኖ ፕሮጀክቶች፣ እንዲሁም የመገጭ ፕሮጀክትና ሌሎችም ይገኙበታል።