በዓለም ዋንጫው እስከ አሁን የትኞቹ አገራት 16ቱን ተቀላቀሉ?

114

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ሕዳር 20 /2015 በኳታር አስተጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ዛሬ 10ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።

32ቱም የዓለም ዋንጫው ተሳታፊ አገራት ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን አድርገዋል።

በምድብ አራት የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ፈረንሳይ በዘንድሮው ውድድር 16ቱን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ አገር ናት።

ፈረንሳይ አውስትራሊያን 4 ለ 1 እንዲሁም ዴንማርክን 2 ለ 1 በመርታት ስድስት ነጥብ በማግኘት አንድ ጨዋታ እየቀራት ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች።

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ብራዚልና ፖርቹጋል ፈረንሳይን ተከትለው 16ት ውስጥ መግባታቸውን ያረጋገጡ አገራት ናቸው።

በምድብ ስምንት ፖርቹጋል ኡራጓይን 2 ለ 0 በምድብ ሰባት ብራዚል ስዊዘርላንድን 1 ለ 0 በማሸነፍ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።

16ት ውስጥ የሚገቡ ቀሪ 13 አገራት ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚደረጉ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች የሚለዩ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም