በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዲፕሎማቶች የኢፌዴሪ አየር ኃይልን ጎበኙ

266

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 19 ቀን 2015 በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዲፕሎማቶች የኢፌዴሪ አየር ኃይልን ጎበኙ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ለመካከለኛና ነባር ዲፕሎማቶች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ትናንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ስልጣኖቹ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እና የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሰልጣኞቹ በዛሬው ዕለትም የኢፌዴሪ አየር ኃይልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም