በአማራ ክልል" የሌማት ትሩፋት" ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል" የሌማት ትሩፋት" ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው
209
ቻግኒ ኢዜአ ህዳር 18 ቀን 2015 በአማራ ክልል "የሌማት ትሩፋት" ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በቻግኒ ከተማ ይፋ እየተደረገ ነው።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋል፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሌማት ትሩፋት ተመጣጣኝ ምግብ በብዛት እና በጥራት በገበያው እንዲኖር በማድረግ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ የምግብ ስርዓት መዘርጋትን አላማ ያደረገ እንደሆነ ተመላክቷል።
የሌማት ትሩፋት የክልሉን የእንስሳት ሃብት ምርታማነት በማሳደግ የሁሉንም ዜጎች የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል የሚያግዝ ነውም ተብሏል።
በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ማር እና ወተት የቅንጦት ምግቦች ሳይሆኑ አቅርቦቱን በማስፋት ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመገንባት ጭምር ታሳቢ በማድረግ የጀመረ ፕሮግራም ነው።
የሌማት ትሩፋት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መሪነት በዚህ ወር ይፋ መደረጉ ይታወቃል።