በመሬት ላይ ሲደረግ በቆየ የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ37 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

158

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 16 ቀን 2015 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ዝርፍያ ጋር በተያያዘ ሲያደርገው በቆየው የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ፤ የክፍለ ከተማ በመሬት ጉዳይ ይወስኑ የነበሩ አመራሮች፤ ባለሙያዎች፤ ደላሎችና ከህብረተሰቡ በድርጊት የተሳተፉትን ጨምሮ 37 ሰዎችን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 12 ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ቀሪዎቹን ግለሰቦችም ፖሊስ ክትትል እያደረገባቸው እንደሚገኝ የተመላከተ ሲሆን ተጨማሪ የማጥራት ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል::

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችም

1. ለምለም አባይነህ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፃሚ

2. አቶ ከፍያለው አሰፋ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

3. አቶ ዋሲሁን ሰውነት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

4. አቶ ኢብራሂም ሀሰን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

5. አቶ ሃይለየሱስ ደስታ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

6. አቶ ዳዊት ከልሌ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ

7. አቶ ልኡልሰገድ ታደሰ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ

ከመንግስት ተቋማት ውጪ በጉዳዩ ተሳታፊነት በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች

8. አቶ አየለ ጉቱ

9. አቶ ጎሳዬ ደሜ

10. አቶ በፍቃዱ ወንደሰን

11. አቶ ሮባ ደበሌ

12. አቶ መታሰቢያ አባተ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም