ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ1 አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ1 አሸነፈች
193
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 13 ቀን 2015 በኳታር እየተካሄደ ባለው የ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ 1 በሆነ ጎል አሸንፋለች።
በምድብ ሶስት 80 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ሉሳይል ስታዲየም አርጀንቲና ከሳዑዲ አረቢያ ባደረጉት ጨዋታቸውን አድርገዋል።
ሳሌህ አልሼህሪ እና ሳሌም አልዳውሳሪ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሩት አንድ አንድ ጎል ነው የሳዑዲ አረቢያ ብሄራዊ ቡድን ድል የቀናው።
አምስተኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎውን የሚያደርገው አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ለሀገሩ በመጀመሪያው አጋማሽ በፍጹም ቅጣት ምት ጎል ማስቆጠር ቢችልም ብሄራዊ ቡድኑን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም።