በ974 የመርከብ ዕቃ ማጓጓዣ ኮንቴነሮች የተሰራው የመጀመሪያው የዓለማችን ተንቃሳቃሽ ስታዲየም

212

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 13 ቀን 2015 22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

ኳታር ለዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ስምንት ስታዲየሞች ያሰናዳች ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሰባቱ አዲስ ናቸው።
አዲስ ከተገነቡት ስታዲየሞች መካከል ስታዲየም ደግሞ 974 ይገኝበታል።

ስያሜያውን ያገኘው የተሰራው ድጋሚ ጥቅም ላይ ከዋሉ 974 የመርከብ ዕቃ ማጓጓዣ ኮንቴነሮች በመሆኑ ነው።

በተጨማሪም የስታዲየሙ ስያሜ የኳታር የስልክ መለያ ቁጥር የሚጀመረው +974 ከመሆኑ ጋር ይያያዛል።

የስታዲየሙ ንድፈ ሀሳብ የተዘጋጀው ‘ፌንዊክ ኢሪባረን አርክቴክት’ የተሰኘ የሕንጻ ዲዛይን ድርጅት ነው።

የተወሰኑት ኮንቴነሮች የፋይናንስ አገልግሎት መስጫዎችና መኪና ማቆሚያዎች አሉት።

ኳታር ግንባታው እ.አ.አ 2018 ተጀምሮ እ.አ.አ 2021 የተጠናቀቀውን ስታዲየም የመርከብ እቃ ማጓጓዣ ኮንቴነሮችና መቀመጫዎች ዓለም ዋንጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ለሌሎች አገራት ለመሸጥ አቅዳለች።

ይህም ስታዲየም 974ን በፊፋ ዓለም ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያ ጊዜያዊ ስታዲየም ያደርገዋል።

በቀላሉ የሚነቃቀለውን ስታዲየም መልሶ በድጋሚ መገጣጣም ይቻላል።

ስታዲየሙ በውሃ ዳርቻ አቅራቢያ የሚገኝ ነው።

የስታዲየሙ ግንባታ ዓላማ ውስን ግብአቶችን መጠቀም እንዲሁም ብክለትና ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ ጋዞችን መቀነስ እንደሆነ ተገልጿል።

ስታዲየም 974 ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰአት በምድብ አራት ሜክሲኮ ከፖላንድ የሚያደርጉትን ጨምሮ ሰባት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም