እየጣለ ያለው ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች አደጋ ሊያስከትል ይችላል

159
አዲስ አበባ ግንቦት 11/2010 በተለያዩ አካባቢዎች እየጣለ ያለው ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንዳስታወቁት በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በበልጉ ወቅት ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል። በዚህ ሳቢያ ቅጽበታዊ የጎርፍ አደጋ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የሚቲዎሮሎጂ ትንበያ ያሳያል። በተለይም በድሬዳዋ፣ በሀረር፣ በመካከለኛው የአገሪቱ አካባቢ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም በደቡብና በኦሮሚያ ከፍተኛ ዝናብና ጎርፍ ሊኖር እንደሚችል ትንበያው ያመለክታል። በረባዳ ቦታዎች በየአካባቢው ባሉ ተፋሰሶችና በወንዞች አካባቢ አደጋው ከፍተኛ ሊሆን ስለሚችል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደረግ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም