በዓለም ዋንጫ እንግሊዝ ኢራንን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈች

185

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ሕዳር 12 ቀን 2015 በ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ዛሬ በምድብ ሁለት በተደረገ ጨዋታ እንግሊዝ ኢራንን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች።

ቡካዮ ሳካ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ራሂም ስተርሊንግ፣ ጁዲ ቤሊንግሃም፣ማርከስ ራሽፎርድና ጃክ ግሪሊሽ የተቀሩትን ጎሎች ለሶስቱ አናብሰት ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው።

ሜህዲ ታሬሚ ለኢራን በጨዋታና በፍጹም ቅጣት ምት 2 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በምድብ ሁለት ዛሬ ከምሽቱ 4 ሰአት አሜሪካ ከዌልስ በአህመድ ቢን አሊ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ከሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ቀደም ብሎ በምድብ አንድ አፍሪካዊቷ አገር ሴኔጋል ከኔዘርላንድስ ከምሽቱ 1 ሰአት በአል ቱማማ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ትናንት በዓለም ዋንጫው መክፈቻ በምደብ አንድ በተደረገ ጨዋታ ኢኳዶር አዘጋጇን አገር ኳታርን 2 ለ 0 ማሸነፏ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም