የኦሮሚያ ክልል የልማት ድርጅቶች ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስረታ እየተካሄደ ነው

145

ህዳር 08/2015 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል የልማት ድርጅቶች ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስረታ እየተካሄደ ነው።

በክልሉ ያሉ የልማት ድርጅቶች የሚመሰርቱት ኢንቨስትመንት ግሩፖች ስድስት መሆናቸው ተገልጿል።

ግሩፖቹም "ኦ ፕሮዱስ፣ ኦሮ አሴምብሊ፣  ኦሮሚያ አግሮ ግሩፕ፣ ቱምሳ ዴቬሎፕመንት፣ ኦሮ ኮንስትራክሽን እንዲሁም  ኦ ማይኒንግ  የተባሉት ናቸው።

የኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስረታ ዓላማም ዘርፉን በአግባቡ ለመምራትና ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩትን አንድ ላይ ለማሰባሰብ እንዲሁም የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ለማፋጠን መሆኑ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሸመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሚኒስቴሮች፣ የክልሉ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም