ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ሰብዓዊ ርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎቹ ዛሬ መቀሌ ገብተዋል

296

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 6 ቀን 2015 ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር የመድኃኒት ርዳታ የጫኑ ሁለት ተሽካርካዎቹ መቀሌ ዛሬ መግባታቸውን አስታወቀ።

ተሽከርካሪዎቹ መድኃኒቶች፣ የአስቸኳይ ጊዜና የመጀመሪያ እርዳታ ድጋፍ የጫኑ መሆናቸውን ማህበሩ አመልክቷል።

እርዳታው በትግራይ ክልል ለሚገኙ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች አስቸኳይ የሕክምና ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ለሚሰጡት ሕክምና እንደሚያግዝ ገልጿል።

የቀይ መስቀል ማህበር በቀጣይ ቀናት በአየርና በየብስ የሕክምና፣ የምግብና ሌሎች አስፈላጊ ሰብዓዊ ርዳታዎችን ወደ ክልሉ እንደሚያጓጉዝ ጠቁሟል።

መንግስት የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።

ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ድጋፍ ክፍት መሆናቸውን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት መግለጹ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም