ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽናል ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ ጎበኙ

104

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 2/2015 ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘውን የአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽናል ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ መጎብኘታቸው ተገለጸ፡፡

ከንቲባዋ ዛሬ በነበራቸው ጉብኝት የኤግዚቢሽን ማዕከሉ የግንባታ አፈፃፀም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ ያስችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከንቲባ አዳነች መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጻ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ግንባታው እንዲፋጠን የከተማዋ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረጉን ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም