ጉባዔው ህዝቡ የሚጠብቀው ውሳኔዎች የሚተላለፉበትና አዳዲስ አመራሮች ወደፊት የሚመጡበት ነው- የህወሓት ሊቀመንበር

60
መስከረም 16/2011 የህወሓት ድርጅታዊ ጉባዔ ህዝቡ የሚጠብቀው ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እና አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት የሚመጡበት እንደሚሆን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዮን  ገ/ሚካኤል ተናገሩ፡፡ ሊቀመንበሉ  በ13ኛው የድርጅቱ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት  ህውሓት ባለፉት ዓመታት ከሌሎች ድርጅቶችና ከህዝቡ ጋር ባደረገው ትግል ህገ መንግስታዊ  ስርዓት እንዲተገበር በማድረግ በሀገሪቱ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖቲካዊ ዘርፎች ውጤቶች ተመዝግቧል። ህወሓት በላፉት 27 ዓመታት በክልሉ በገጠርም ሆነ በከተማ ህብረተሰቡን ከድህነት ለማላቀቅ በርካታ ስራዎች አከናውኗል ነው ያሉት፡፡ በክልሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ህብረተሰቡን  ከድህነት ለማላቀቅ  ድርጅቱ  ለመድረስ  ባቀደው መሰረት  ወደፊት እንዳይጓዝ እንቅፋት  ሆነዋል ብለዋል። “ህወሃት ራሱን ፈትሾ የማስተካከል የቆየ ባህል ያለው ድርጅት ነው” ያሉት ዶክተር  ደብረፂዮን   ከችግሩ  ለመውጣትም ጥልቅ ተሃድሶ ሲያካሂድ ቆይቷል ብልዋል፡፡ ጉባኤው  የትግራይ ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ ጋር  ከ20 ዓመታት በኋላ አዲስ ዓመት በጋራ ባከበሩበት ማግስት  መካሄዱ ልዩ ያደርገዋልም ብለዋል። “የትግራይ እና የኤርትራ ህዝብ በታሪክ፣ቋንቋ እና  ባህል  የተሳሰሩ ናቸው” ያሉት ዶክተር ደብረፂዮን  ባለፉት ዓመታት የባከኑትን እድሎች በማካካስ  በጋራ  እንደሚሰሩም  ገልፀዋል። ጉባኤው  ድርጅቱ ባለፉት ዓመትት ከነበሩት ጉድለቶች በመማር ወደፊት ለተሸለ ስራ ጠንክሮ የሚወጣበት  አቅጠጫ ይቀመጥበታልም ብለዋል። በጉባኤው የክልሉ ህብረተሰብ የሚጠብቀው ውሳኔዎች የሚተላለፉበት አና አዳዲስ አመራሮች ወደፊት የሚመጡበት እንደሚሆንም ዶክተር ደብረፂዮን ተናግረዋል፡፡ የጉባኤው ተሰታፊዎችም  የሰማዕታትን አደራ በማክበር የህዝብ ችግር የሚፈቱ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ የራሳቸውን ሚና  እንዲወጡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ የፌዴራል ሥርዓቱ የተለያዩ ችግሮች እየገጠሙት ነው ያሉት  ሊቀመንበሩ፤ ብሄርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እና ግጭት አንዱ ማሳያ  እንደሆነም ገልፀዋል። በቅርቡ  ቡራዩ እና አከባቢው የተፈፀው ድርጊት ተቀባይነት እንደሌለው የገለፁት ዶክተር ደብረፂዮን  ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም ህወሓት የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም