የሰቆጣ ከተማና አካባቢው እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

166

ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም ሰቆጣ (ኢዜአ) በሰቆጣ ከተማና አካባቢው ለ15 ወራት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በዛሬው እለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰቆጣ አገልግሎት መስጫ ማእከል አስታወቀ።

የማእከሉ ሃላፊ አቶ ኪሮስ ፈረደ ለኢዜአ እንደገለፁት ሃምሌ 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሰቆጣ ከተማን ጨምሮ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የሚገኙ ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡን አውስተዋል።

በዚህም ከአዲስ አበባ ፣ ከባህር ዳርና ወልደያ ዲስትሪክት በተወጣጡ ባለሞያዎች ሌሊትና ቀን ባከናወኑት የጥገና ስራ ሰቆጣና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ በኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ይደርስ የነበረው እንግልትና የኢኮኖሚ ጫና ያቃልላል ብለዋል።

በኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች በተደረገ ርብርብ ላሊበላ ፣ቆቦ፣ አላማጣና በአካባቢው የሚገኙ ወረዳዎች ከቀናት በፊት የመብራት አገልግሎቱ ተጠቃሚ መደረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም