የሰላም ስምምነቱ አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ ምስክርነት የሰጠ ነው- ምክር ቤቱ

131

(ኢዜአ) ጥቅምት 25 ቀን 2015 የሰላም ስምምነቱ አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ ምስክርነት የሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የሰላም ስምምነቱ የሚደገፍና ለኢትዮጵያ ህዝቦች እፎይታ የሰጠ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያን ሰላም የማይሹ ታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ ያከሸፈና ለዘላቂ ሰላም ዕድል የሰጠ መሆኑን በመጥቀስ፡፡

በመሆኑም ስምምነቱ ፍሬያማ እንዲሆን የፖለቲካ ሃይሎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች መልሶ ለማቋቋም እና አካባቢዎቹን መልሶ ለመገንባት ሁሉም ዜጋ ርብርብ ማድረግ እንዳለበትም ጠይቋል፡፡

በፖለቲካ ልሂቃን፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እና ፖለቲከኞች ከምንጊዜውም በላይ ለዘላቂ ሰላም ሊሰሩ እንደሚገባም ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም