ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከኮትዲቯር አቻቸው ጋር ተወያዩ

148

ጥቅምት 24 ቀን 2015 (ኢዜአ) ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከኮትዲቯር አቻቸው አላሳን ኦታራ ጋር በኮትዲቯር አቢጃን ከተማ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማድነቅ በቀጣይ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በተጨማሪም በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ማዕቀፎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በኮትዲቯር እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም