የአፍሪካ ህብረት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል

215

ጥቅምት 24 2015 (ኢዜአ) የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ማህማት ሕብረቱ የኢትዮጵያ መንግስትና ሕወሓት ለደረሱበት የሰላም ስምምነት ዘላቂነት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ።

ኮሚሽነሩ በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት ሲካሄድ በነበረው የሰላም ውይይት የግጭት ማቆም ስምምነት ለተፈራረሙት ወገኖች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ሕብረቱ መንግስትና ሕወሓት በደረሱበት ስምምነት መሰረት ዘላቂ ሰላምን እንዲያስቀጥሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ትላንት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሓት መካከል ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያከበረና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስጠበቀ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም