አፍሪካ ያላትን ዐቅም አገናዝበው ልትሆን የሚገባትን የሚቀምሩላት ወጣት ልጆቿ ናቸው--ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

114

ጥቅምት 22 ቀን 2015 (ኢዜአ) አፍሪካ አሁን የሆነችውን ብቻ ሳይሆን፣ ያላትን ዐቅም አገናዝበው ልትሆን የሚገባትን የሚቀምሩላት ወጣት ልጆቿ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ፓንአፍሪካዊነትን በአመራራቸው የገለጡ የትናንት ፈር ቀዳጆች ለዚህ ጽኑ መሠረትን ጥለዋል ነው ያሉት።

አህጉራችን ያላትን ዐቅም ተጠቅማ ለሁሉም ዜጎቿ ምቹ እንድትሆን ማስቻል በተለይም ከአፍሪካውያን ወጣት መሪዎች እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ "ስለዚህም የተጣለባችሁን ተስፋ እውን እንድታደርጉት አደራ እላለሁ ሲሉ መልእክታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

የመጀመሪያው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ መርሐ-ግብሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የቀድሞ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር በተገኙበት ተካሂዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም