2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

235

ጥቅምት 22/2015(ኢዜአ) የጉምሩክ ኮሚሽን 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዙን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌደራል ፖሊስ፣ገቢዎች ሚኒስቴር እና ፍትህ ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የኮንትሮባንድ መከላከል ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ተገኔ ደረሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት የኮንትሮባንድ ወጪና ገቢ ዕቃዎችን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

በዚህም ግምታዊ ዋጋቸው 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ነው የጠቀሱት።

አደንዛዥ ዕፅ፣ የግብርና ምርቶች፣ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሊወጣ የነበረ ገንዘብ ከተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በኮንትሮባንድ ተግባር የተሳተፉ 351 ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ነው ያነሱት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም