ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ምእራፍ ሁለት የወዳጅነት ፓርክ የበርካታ ጥንዶች የጋብቻ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

288

ጥቅምት 20/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በምእራፍ ሁለት የወዳጅነት ፓርክ የበርካታ ጥንዶች የጋብቻ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት የሸገር ፓርክ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት አካል በሆነው የወዳጅነት ፓርክ ሲመረቅ በሠርግ ዐጸዱ ላይ ጥንዶች ሰርጋቸውን እንዲያካሂዱ ልዩ ስጦታ ማቅረቡን ተገልጿል።

ስጦታውም ጋብቻቸውን ለመፈጸም የተዘጋጁ ወይም አቅደው ሳይሳካላቸው የቆዩ 50 ጥንዶችን በመሥፈርት መርጦ የጋብቻ ሥርዓታቸውን በሥፍራው እንዲፈጽሙ ማድረግ ነበር።

ይህንን ተከትሎም በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስመረቁት የወዳጅነት ፓርክ ምዕራፍ ሁለት የሰርግ አጸድ ውስጥ የጽህፈት ቤቱን ጥሪ የተቀበሉ በርካታ ጥንዶች የጋብቻ ስነስርዓታቸውን ፈጽመዋል።

በሰርግ መርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም