ግንባታው የተጠናቀቀው የሸገር ማስዋብ ምዕራፍ 2 ፕሮጀክት ለአንድ ሳምንት በነፃ ክፍት ሆኗል

175

ጥቅምት 20/2015 (ኢዜአ) ግንባታው የተጠናቀቀውን የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ለአንድ ሳምንት በነፃ ክፍት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክ ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅትም ግንባታው የተጠናቀቀውን የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይን ለአንድ ሳምንት በነፃ ክፍት መሆኑን አብስረዋል።

ወላጆችም የሸገርን የማስዋብ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ለአንድ ሳምንት በነፃ በሚቆየው ጉብኝት መርሃ-ግብር ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣት ማዝናናት እንደሚቸሉ ጠቁመዋል።

May be an image of 9 people, people standing, people playing sports and grass

ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይ በአብርሆት ቤተ መጽኃፍት እና በዋናው የወዳጅነት አደባባይ መካከል ይገኛል።

አደባባዩም ደረጃውን የጠበቀ የህፃናት መዝናኛ፣ ጥንዶች የሰርግ ፎቷቸውን የሚነሱበት፣ የቅርጫትና እጅ ኳስ መጫዎቻ፣ ካፌ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ክዋኔዎች የሚደረጉበት ማራኪ መዝናኛ ስፍራዎችን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም