ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይን መርቀው ከፈቱ

406

ጥቅምት 20/2015 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይ በአብርሆት ቤተ መጽኃፍት እና በዋናው የወዳጅነት አደባባይ መካከል ይገኛል።

አደባባዩም ደረጃውን የጠበቀ የህፃናት መዝናኛ፣ ጥንዶች የሰርግ ፎቷቸውን የሚነሱበት፣ የቅርጫትና እጅ ኳስ መጫዎቻ፣ ካፌ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ክዋኔዎች የሚደረጉበት ማራኪ መዝናኛ ስፍራዎችን ይዟል።

ይሄ ልዩ አደባባይ ለመጪው አንድ ሳምንት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረግም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም