ሠራዊቱ አሸባሪው ህወሃት በኮረም አካባቢ ያፈረሳቸውን ድልድዮችና መንገዶች ጠገነ

194

ጥቅምት 17/2015(ኢዜአ) መከላከያ ሠራዊት አሸባሪው ህወሃት በኮረም አካባቢ ያፈረሳቸውን መንገዶችና ድልድዮች በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

በኮረም ግዳጅ ቀጠና የሚገኘው የዕዝ መሐንዲስ የሠራዊቱን ግዳጅ እና የአካባቢውን ህዝብ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ መንገዶችናና ድልድዮችን በመጠገን ለአገልግሎት እያበቃ መሆኑን ኃላፊ ኮሎኔል ክፍሌ ሊቨን ገልፀዋል።

የዕዙ መሃንዲስ ክፍል አሸባሪው ህወሃት ያፈረሳቸውን ድልድዮች በመስራት እና የመንገድ ብልሽቶችን በፍጥነት በማስተካከል ለአካባቢው ማህበረሰብ ምቹ እንቅስቃሴ ፈጥሯል ነው ያሉት።

አሸባሪው ህወሓት የመንግስት እና የህዝብ ሀብት በማውደም፣ ድልድዮችን በማፈራረስ እና መንገዶችን በመሰናክል ቢዘጋም ሠራዊታችንን ማስቆም አልቻለም ብለዋል።

ሠራዊታችን ግዳጁን በስኬት እንዲወጣ መሃንዲስ ክፍሉ ከፍተኛ አስተወፅኦ እያደረገ ነው ያሉት ኮሎኔል ክፍሌ ብቁ የመሃንዲስ ሙያተኞችን በመጠቀም ዘመናዊ ድልድዮችን አገልግሎት ላይ በማዋል ለድል የሚያበቁ አመርቂ ስራዎች ተከናውኗል ብለዋል።

አክለውም አሸባሪው ህወሃት የለኮሰውን ጦርነት በድል አድራጊነት ለማጠናቀቅ መሃንዲስ ክፍሉ በተሟላ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም