ሰራዊቱ ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር የሚያደርገውን ተጋድሎና ድል በሌሎች መስኮች በመድገም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሉዊጂ ገለጹ

123

ጥቅምት 15/2015 (ኢዜአ) መከላከያ ሰራዊት ለአገር ሉዓላዊነት መከበር የሚያርገውን ተጋድሎና ድል በሌሎች መስኮች በመድገም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዋጂ ተናገሩ።

የመከላከያ ሰራዊት ቀን ዛሬ ጥቅምት 15/2015 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅት እየተከበረ ይገኛል።

May be an image of 4 people, people sitting, people standing and indoor

ሚኒስትር ድኤታዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚጠይቀውን ብርታትና ፅናት ይዞ ለአገር ሰላም፣ ሉዓላዊነት መከበርና የግዛት አንድነት መጠበቅ ዋጋ እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሠራዊቱ ያለውን የደጀንነት ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን የሚመጥን ብቁ ሰራዊት እየተገነባ ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታዋ ወታደራዊ አስተማማኝ ዝግጁነት ያለውና ጦርነትን ከሩቅ የሚያስቀር የሰራዊት አቅም መገንባትም እንዲሁ።

ሰራዊቱ ከሀገር አልፎ በሰላም ማስከበር ዓለም አቀፍ ተልዕኮን በብቃት የሚወጣ ሆኖ እየተገነባ መሆኑን በመግለጽ ለህዝብ የከፈለውና እየከፈለ ያለው መሰዋዕትነት ሊመለስና እና በቃላት ሊገለጽ ባይችልም ሰራዊቱን መዘከርና ማክበር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

“ቀኑን ስናከብር የሰራዊቱን ተጋድሎና ጀግንነት እየዘከርን ሌላ ታሪክ ለመጻፍ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማቷን አረጋግጣ ቀና ብላ እንድትሄድ ቁርጠኝነት የምናሳይበት መሆን አለበት” ሲሉም ተናግረዋል።

ቀኑ መከበሩና ሰራዊቱ መዘከሩ ሰራዊቱ በቀጣይም በፅናትና ጀግንነት ስንቅ ይዞ እንዲራመድ ሞራል ይሰጠዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም