የመከላከያ ሰራዊት ቀን በፓሽን አካዳሚ በመከበር ላይ ይገኛል

225

ጥቅምት 15/2015 (ኢዜአ) የመከላከያ ሰራዊት ቀን በፓሽን አካዳሚ በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ የአካዳሚው ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የመከላከያ ሰራዊት ቀን "ህዝባችን የጥንካሬያችን ምንጭ" በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ቀን እንደሚከበር መገለፁ ይታወሳል።

አካዳሚው ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲፈራ የሀገር ሰላም ወሳኝ እና ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ለዚህ ደግሞ መከላከያ ሰራዊት እየከፈለ ላለው የህይወት ተጋድሎ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም