ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
135
ጥቅምት 09 ቀን 2015 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ስላለው የግጭት ሁኔታ ተነጋግረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዩናይት ኪንግደም የኢትዮጵያ ጠንካራ የልማት አጋር መሆኗን በመግለጽ ግንኙነቱ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ በበኩላቸው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት መጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ማመልከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።