ኢትዮጵያ እና ህንድ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

108

ጥቅምት 08 ቀን 2015 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ እና ህንድ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ።

የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ በህንድ እየተካሄደ ካለው የአፍሪካ-ህንድ የመከላከያ ጉበኤ ባሻገር ከህንድ አቻቸው ራጃንት ሲንጋ ጋር የጎንዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም በኢትዮጵያ ወታደራዊ የልህቀት ማዕከላትን ለማገዝ ህንድ ቅድሚያ እንደምትሰጥና ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በተለይ በመከላከያ ዘርፉ ያለውን ትብብር የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ በዘርፉ ያለውን ትብብር ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ በመግለጽ በተለይ በሰዋዊ አስተውሎት እና በቴክኖሎጂ ማገዝ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

የህንድ የመከላከያ ሚኒስትር ራጃንት ሲንጋ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ አብረው ለመስራት የሚያስችል እምቅ አቅም አላቸው ብለዋል።

ሚኒስትሩ በዘርፉ ያለውን አቅም ለማሳድግና ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል።

በመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ የተመራው የልኡክ ቡድን በህንድ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአፍሪካ-ህንድ የመከላከያ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም