ዳያስፖራው የተሳተፈበት ግራንድ አፍሪካን ራን በቨርጂኒያ ግዛት ተካሄደ

211

ጥቅምት 6/2015 (ኢዜአ) የዳያስፖራው ማህበረሰብ የተሳተፈበት የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ትናንት በቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ከተማ ተካሂዷል።

"አብሮነት መሻል ነው" በሚል መሪ ሀሳብ በተከናወነው ውድድር ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣አትሌት ፋጡማ ሮባ፣አትሌት ሚሊዮን ወልዴ፣አትሌት ታሪኩ በቀለና አትሌት ቁጥሬ ዱለቻ ተገኝተዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተካፈሉበት ውድድር በአዋቂዎች የአምስት ኪሎ ሜትር እንዲሁም በሕጻናት የአንድ ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄዷል።

በዕለቱ በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ የሚመራው ሕብረት ለበጎ የጎ አድራጎት ድርጅት ለሚያሰራው የኩላሊት ሕክምና ሆስፒታል ገቢ ተሰብስቧል።

የዘንድሮው ግራንድ አፍሪካን ራን ለአራተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮች ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት መዋላቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም