ከአፍሪካ የተለያዩ አገሮች የመጡ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

125

መስከረም 28 ቀን 2015(ኢዜአ) ከአፍሪካ የተለያዩ አገሮች የመጡ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ።

ሙዚየሙን የጎበኙት ጋዜጠኞች ከጋና፣ ካሜሮን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኒጀርና ሌሎች አገሮች የተውጣጡ ናቸው።

በጉብኝታቸው ባዩት ነገር መደሰታቸውን በመግለፅ ኢትዮጵያ ለሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቷን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ይህ የኢትዮጵያ መልካም ተሞክሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲስፋፋ በዘገባዎቻቸው እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

በመሃል አዲስ አበባ በአስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ማራኪ ጉልላት ይዞ የተገነባው የሳይንስ ሙዚየም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል።

ሙዚየሙ ሳይንስና ጥበብን በጋራ አጣምሮ በያዘ የኪነ-ህንጻ ንድፍ የተገነባ ሲሆን፤ ኪነህንጻው የያዘው ክብ ቅርፅም በማያቋርጥ ሂደት ውስጥ ያለ እድገትንና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት  የሚያሳይ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም