1497ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) የመውሊድ በዓል በደቡብ ወሎ ዞን "ጀማ ንጉስ" መስጅድ በድምቀት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
1497ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) የመውሊድ በዓል በደቡብ ወሎ ዞን "ጀማ ንጉስ" መስጅድ በድምቀት እየተከበረ ነው
353
ደሴ መስከረም 28/2015 (ኢዜአ) 1497ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) የመውሊድ በዓል በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ "ጀማ ንጉስ" መስጅድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን ህብረተሰቡ የመውሊድን በዓል ሲያከብር አንድነቱን በማጠናከር አቅመ ደካሞችን በመንከባከብና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
1497ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) የመውሊድ በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።