እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

269

መስከረም 28/2015 (ኢዜአ) በነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) መወለድ ዓለም እጅግ ተጠቅማለች። የዓለምን ታሪክ ቀይረዋል።

የሰው ልጆችንም ሕይወት ለውጠዋል።የመውሊድን በዓል የምናከብረው የዓለምን ታሪክና የሰው ልጆችን ሕይወት በመለውጥ መሆን አለበት።

በግብርና እና በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ እየሠራን ያለው ሥራ የሀገራችንን ታሪክና የሕዝባችንን ሕይወት የሚለውጥ ነው።

ኢትዮጵያን ከጦርነት በመገላገል ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ታሪክና ሕይወት ወደሚለውጡ ዕቅዶቻችን እንዞራለን።

የጀመርነው "የሌማት ትሩፋት" የቤተሰቦቻችንን ሥርዓተ ምግብ እንዲለውጥ ተግተን እንድንሠራ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁን ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም